Blog

የኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ መሣሪያዎች

የጅማት ሙዚቃ መሣሪያዎች

እነዚህ መሣሪያዎች ድምጽ የሚሰጡት በንዝረት ነው።

 • በገና፡ መንፈሳዊ ዜማዎችን ለማዜም በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ የሙዚቃ መሣሪያ ነው።
 • ክራር፡ ይህ የጅማት የሙዚቃ መሣሪያ ለአያሌ ዓመታት ለደስታ፣ ለትካዜ፣ ለፍቅርና ለቀረርቶ ስንጠቀምበት የቆየ መሣሪያ ነው።
 • መሰንቆ (ማሲንቆ)፡ በተለይ በሰሜን ኢትዮጵያ የሚገኝ ጥንታዊ የሙዚቃ መሣሪያ ነው።
 • ዲታ፡ በሲዳሞ የሚገኝ የጅማት መሣሪያ ነው።
 • ዱል፡ በጋምቤላ የሚገኝ የጅማት መሣሪያ ነው።

የትንፋሽ ሙዚቃ መሣሪያዎች

እነዚህ መሣሪያዎች ድምጽ የሚሰጡት በትንፋሽ ኃይል ነው።

 • ዋሽንት፡ አብዛኛውን ጊዜ እረኞች በሀገር ቤት ይገለገሉበታል። በተጨማሪም በመድረክ ላይ ለክራርና ለመሰንቆ ቅኝት በመስጠትና ዜማን በማጀብ ያገለግላል።
 • አምቢልታ፡ ሶስት ዓይነት አመቢልታዎች አሉ። ስማቸውም ኡፍን፣ አውራ እና የማ ነው። በኢትዮጵያ ለክብረ በዓልና ወደ ጦር ሜዳ ለሚሄድ ሰልፈኛ የሚነፋ አድማቂ መሣሪያ ነው።
 • መለከት፡ ቀደም ባለው ጊዜ ሰዎች ተሰብስበው የመንግሥት አዋጅ እንዲሰሙ ትዕዛዝን መስጫ መሣሪያ ሆኖ ሲያገለግል የቆየ ነው።
 • ድንኬ፡ በሲዳሞ ክፍለ ሀገር በወላይታ አካባቢ ለአስከሬን ማጀቢያነት የሚያገለግል መሣሪያ ነው።
 • ፖረሬሳ፡ በደቡብ ኢትዮጵያ ለዘፈን ማጀቢያ የሚያገለግል መሣሪያ ነው።
 • ሁራ፡ በከፋ ክፍለ ሀገር ያሉ ጎሳዎች የሚጠቀሙበት የሙዚቃ መሣሪያ ነው።
 • ሁልዱዱዋ፡ በሲዳሞ ክፍለ ሀገር የቀብር ሥነ ሥርዓት ለመግለጽ የሚነፋ መሣሪያ ነው።
 • ጨቻ ዝዬ፡ በደቡብ ኢትዮጵያ ውዝዋዜ ለማድመቅ የሚያገለግል የሙዚቃ መሣሪያ ነው።
 • ዛክ፡ በከፋ ክፍለ ሀገር የሚገኝ የሙዚቃ መሣሪያ ነው።
 • ሸመቶ፡ በከፋ ክፍለ ሀገር የሚገኝ የሙዚቃ መሣሪያ ነው።
 • ፋንፋ፡ በከፋ ክፍለ ሀገርና በጋሞጎፋ /ኮንሶ/ የሚገኝ የሙዚቃ መሣሪያ ነው።
 • አዋዛ፡ በወለጋ ክፍለ ሀገር በአሶሳ አካባቢ የሚገኝ የሙዚቃ መሣሪያ ነው።

የምት ሙዚቃ መሣሪያዎች

 • ከበሮ፡ ለዘፈን ማድመቂያና ለሠርግ እንዲሁም ለቤተ ክርስቲያን ዝማሬ ቀሳውስት በሽብሸባ ጊዜ የሚጠቀሙበት መሣሪያ ነው።
 • አታሞ፡ ለሙዚቃና ለጭፈራ የሚያገለግል መሣሪያ ነው።
 • ነጋሪት፡ በሰልፍ ጊዜ የሚጎሰም የሙዚቃ መሣሪያ ነው።
 • መቋሚያ፡ ለመንፈሳዊ ዝማሬ ከከበሮው ስልት ጋር በተዛመደ ሁኔታ በመንቀሳቀስ ቀሳውስት የሚጠቀሙበት መሣሪያ ነው።
 • ፀናፅል፡ ለመንፈሳዊ ዝማሬ ቀሳውስት የሚጠቀሙበት መሣሪያ ነው።
 • ቅል፡ ቅል በውስጡ ጠጠሮች ወይም ፍሬዎች ተጨምረውበት ለዘፈን ማድመቂያ ያገለግላል።
 • ቻንቻ፡ በጋሞጎፋ ክፍለ ሀገር በጭፈራ ጊዜ በወገብ ላይ የሚታሰር አዳማቂ መሣሪያ ነው።
 • ካመባ፡ ከሸክላ የተሠራ በደቡብና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የሚገኝ መሣሪያ ነው።
 • ቃጭል፡ አብዛኛውን ጊዜ ለመንፈሳዊ ዜማ የሚያገለግል መሣሪያ ነው።
 • ቶሞ፡ በጋምቤላ ብሔረሰብ ውስጥ እውቅና ተወዳጅ የሆነ የሙዚቃ መሣሪያ ነው። በተጨማሪም በኬንያ፣ ኡጋንዳ፣ ታንዛኒያ፣ ናይጄሪያ፣ ሱዳንና ዛየርም በዚህ መሣሪያ እንደሚጠቀሙ ታውቋል።
 • ጋሬ፡ በጋምቤላ ብሔረሰብ ውስጥ በእግር ላይ ታስሮ ጭፈራን የሚያደምቅ የሙዚቃ መሣሪያ ነው።
 • የግመል ቃጭል፡ ይህ መሣሪያ በተለይ ከእንጨት የሚሠራ ሆኖ ሙዚቃን ለማጀብ የሚጠቅም መሣሪያ ነው።
Advertisements

Ethiopian Cultural Accessories

misgana-gebeya-ethiopian-tradition1
ከቅል የሚሰራ የሐረሪ የባህል መገልገያ

ከቅል የሚሰራ የሐረሪ የባህል መገልገያ ጭኮ ፣ ጨጨብሳና ወተት፣ የወተት ተዋፅዎ ማስቀምጫ ለምሳሌ እርጎ ቅቤ ሳይበላሽ ለብዙ ግዜ እንዲቆይ ያደርጋል ። ቡና ለምጠጫነትም የሚገለገሉብት ከቅል የሚሰራው የኸው ሲሆን ስሙም ‘ቁሉ’ በማለት የታውቃል ። ይህ መጠጫ በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞችም ሲጠቀሙበት ይስተዋላል።   በተለይ በኦሮሚያ ክልልና አፋርን ጨምሮ ይጠቀሙበታል ። ይህ ከቅል የሚስራው ለቤት ውስጥ መገልገያነት አልፎ ቤትንም ማስዋቢያም ነው ።

Ethiopian Culture Accessories

misgana-gebeyaethiopian-tradition›

የኢትዮጵያ የባህል የሙዚቃ መሳሪያዎች
1.ጊታር
2.ማሰንቆ
3.በገና
4.መለከት

5.አርጋኖን
6.ከበሮ
7.ጽናጽል
8.ቀረነ መለከት
9.ነጋሪት
10.ዕንዚራ
11.እንቢልታ
12.ዋሽንት ናቸው